ATI Agri-Tech Innovation Competition — የግብርና ሀሳባችሁን ወደ እውነተኛ ቢዝነስ የምትቀይሩበት ዕድል!

ስለ ፕሮጀክቱ

ቀጣዩ ትልቅ የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ፈጠራ በግብርና ዘርፍ ቢመጣስ?

አርሶ አደሮችን ከገበያ ጋር የሚያገናኝ አፕሊኬሽን፣ በAI የሚሠራ የግብርና ምክር ሥርዓት ወይም በድሮንና በሰንሰሮች የተደገፈ የእርሻ መረጃ መፍትሔ ማዘጋጀት ብትችሉስ?

እነዚህ ሀሳቦች ወደ እውነተኛ የንግድ ሥራ ሊቀየሩ ይችላሉ።

በዚህ የዲጂታል ይዘት ፕሮጀክት የኢትዮጵያ የግብርና ሽግግር ኢንስቲትዩት (ATI) ያዘጋጀውን Agri-Tech Innovation Competition ለወጣቶች፣ ለሥራ ፈጣሪዎችና ለቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ለማስተዋወቅ ትኩረት አድርጌያለሁ።

ግብርና እና ቴክኖሎጂ ሲገናኙ

ግብርና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚና ለብዙ ዜጎች የኑሮ መሠረት አስፈላጊ ዘርፍ ነው።

ነገር ግን በምርታማነት፣ በገበያ ተደራሽነት፣ በመረጃ አገኛኘትና በምርት አቅርቦት ላይ የተለያዩ ችግሮች አሉ።

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ቴክኖሎጂ አስፈላጊ አማራጮችን ሊፈጥር ይችላል።

ለምሳሌ አርሶ አደሮችን ከገዢዎች ጋር የሚያገናኙ ዲጂታል መድረኮች፣ የግብርና መረጃ የሚያቀርቡ የሞባይል መተግበሪያዎች እና በAI የተደገፉ የምክር አገልግሎቶች የፈጠራ መፍትሔዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

Agri-Tech Innovation Competition ምንድን ነው?

የAgricultural Transformation Institute (ATI) የግብርና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ለማበረታታት Digital Agriculture Innovation Challenge የተባለ መርሐ ግብር አዘጋጅቷል።

ውድድሩ በግብርና ዘርፍ ላይ የሚታዩ እውነተኛ ችግሮችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለመፍታት የሚፈልጉ ሥራ ፈጣሪዎችንና ስታርትአፖችን ለመደገፍ የተዘጋጀ ነው።

ዓላማው ጥሩ ሀሳብ ያላቸውን ወጣቶች ማወዳደር ብቻ ሳይሆን፣ ሀሳቦቻቸውን ወደ ተግባራዊ ምርትና አገልግሎት እንዲቀይሩ ማገዝም ነው።

ከሀሳብ እስከ ተግባራዊ መፍትሔ

የATI Innovation Challenge በአራት ዋና ደረጃዎች የተዋቀረ ነው።

የመጀመሪያው የግብርና ችግሮችን መለየት ነው። በመቀጠል ተሳታፊዎች ሀሳቦቻቸውን የሚያሻሽሉበት Innovation Sprint ይካሄዳል።

ሦስተኛው Incubation ሲሆን የባለሙያዎች ምክር፣ የቴክኒክ ድጋፍና የቢዝነስ ልማት እገዛ ይሰጣል።

የመጨረሻው ደረጃ Commercialization የሚባል ሲሆን የተመረጡ መፍትሔዎችን ወደ ገበያ ለማቅረብ ያግዛል።

በመጀመሪያው ዙር 372 ማመልከቻዎች የቀረቡ ሲሆን፣ 50 ስታርትአፖች ለመጀመሪያ ደረጃ የፈጠራ ሥልጠናዎች ተመርጠዋል። ከእነዚህም 20 ስታርትአፖች ወደ Incubation ደረጃ አልፈዋል።

የይዘት አቀራረብ

ይህንን ቪዲዮ ሳዘጋጅ ዋና መልዕክቴ ቀላል ነበር።

የግብርና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ሀሳብ ካላችሁ፣ ሀሳቡን ብቻ ይዛችሁ አትቀመጡ። ወደ ተግባር ለመቀየር ያሉ ዕድሎችን ፈልጉ!

ወጣቶች በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸ