Samsung Galaxy S26 Ultra — ከጎንዎ ያለ ሰው የስልክዎን ስክሪን ማየት ባይችልስ?

ስለ ፕሮጀክቱ

በአውቶቡስ፣ በካፌ ወይም በሌላ የሕዝብ ቦታ ስልካችሁን ስትጠቀሙ ከጎናችሁ ያለ ሰው ስክሪናችሁን ለማየት ሲሞክር አጋጥሟችኋል?

የስልካችሁ ስክሪን ለእናንተ ግልጽ ሆኖ ለሌሎች ሰዎች ከጎን ሲያዩት በቀላሉ የማይነበብ ቢሆንስ?

Samsung Galaxy S26 Ultra ይህንን የሚያስችል Privacy Display የተባለ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ይዞ ቀርቧል።

በዚህ የቴክኖሎጂ ግምገማ ፕሮጀክት የስልኩን አዲስ የግላዊነት መጠበቂያ ስክሪን፣ የሥራ ሂደቱን እና ለተጠቃሚዎች ያለውን ጥቅም በቀላል መንገድ ለማስረዳት ትኩረት አድርጌያለሁ።

Privacy Display ምንድን ነው?

ከዚህ በፊት የስልካችንን ስክሪን ከሌሎች ለመደበቅ Privacy Glass የሚባል ተጨማሪ የስክሪን መከላከያ መለጠፍ የተለመደ ነበር።

ነገር ግን Samsung Galaxy S26 Ultra ይህንን ቴክኖሎጂ በስክሪኑ ውስጥ አካትቶ አቅርቦታል።

Privacy Display ሲነቃ ስክሪኑን ከፊት የሚመለከተው ተጠቃሚ ይዘቱን ማየት ይችላል። ከጎን የሚመለከቱ ሰዎች ግን የስክሪኑን ይዘት ለማንበብ ይቸገራሉ።

ባህሪውን ማጥፋትና ማብራትም ይቻላል።

ይህ ቴክኖሎጂ እንዴት ይሠራል?

Samsung በዚህ ስክሪን ውስጥ Flex Magic Pixel የተባለ ቴክኖሎጂ ይጠቀማል።

ይህ ቴክኖሎጂ ከስክሪኑ ፒክሰሎች የሚወጣው ብርሃን በምን አቅጣጫ እንደሚሰራጭ ይቆጣጠራል።

በመደበኛ ሁኔታ ስክሪኑን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ማየት ይቻላል።

Privacy Display ሲነቃ ግን ይህ የእይታ አቅጣጫ ይገደባል። በዚህም ከጎን ያሉ ሰዎች የሚያዩት መረጃ ይቀንሳል።

የተለያዩ የግላዊነት አማራጮች

ከሚያስደንቁት ባህሪያት አንዱ Privacy Display ለሁሉም ስክሪን ብቻ ሳይሆን ለተወሰኑ አገልግሎቶችም መዘጋጀት መቻሉ ነው።

ለምሳሌ የተወሰኑ አፕሊኬሽኖችን ስንከፍት፣ የስልካችንን Password ስናስገባ ወይም የNotification መልዕክቶች ሲመጡ የግላዊነት መከላከያው በራሱ እንዲነቃ ማድረግ ይቻላል።

ይህ በተለይ የግል መረጃዎችን ወይም የባንክ አገልግሎቶችን ስንጠቀም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።

የይዘት አቀራረብ

በዚህ ቪዲዮ ዋና መነሻዬ ለብዙ ሰዎች የሚታወቅ አንድ ተሞክሮ ነው።

ስልካችንን ስንጠቀም ከጎናችን ያለ ሰው የምናየውን ነገር ለምን ማየት አለበት?

ይህንን ጥያቄ በመጠቀም የSamsung Galaxy S26 Ultra Privacy Display ባህሪን ለተመልካቾቼ በቀላልና ማራኪ መንገድ ለማቅረብ ሞክሬያለሁ።

የቴክኖሎጂውን አሠራር ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር በማገናኘት ለተጠቃሚዎች ያለውን ጠቀሜታ ለማሳየት ነበር ዓላማዬ።

Privacy Display ሙሉ በሙሉ ይከላከላል?

Privacy Display ከጎን የሚታየውን መረጃ ለመቀነስ የሚረዳ ቢሆንም፣ በሁሉም ሁኔታ 100% የግላዊነት ጥበቃ ይሰጣል ማለት አይደለም።

የስክሪኑ ብርሃን፣ የሰውየው የመመልከቻ አቅጣጫ እና የአካባቢው ብርሃን በውጤቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።

Maximum Privacy Protection ሲነቃም የስክሪኑ ብርሃንና ቀለም በመጠኑ ሊለወጡ ይችላሉ።

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

የስማርትፎን እድገት ሁልጊዜ በትልቅ ካሜራ፣ በፈጣን ፕሮሰሰር ወይም በትልቅ ባትሪ ብቻ አይለካም።

አንዳንድ ጊዜ ትልቅ ፈጠራ በዕለት ተዕለት አጠቃቀማችን ውስጥ የሚያጋጥመንን ቀላል ችግር መፍታት ነው።

የSamsung Galaxy S26 Ultra Privacy Display ባህሪም የዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው።

በዚህ ፕሮጀክት ቴክኖሎጂ ግላዊነታችንን ለመጠበቅ እንዴት ሊረዳ እንደሚችል ለኢትዮጵያ ተመልካቾች በቀላል ቋንቋ ለማስረዳት ትኩረት አድርጌያለሁ።

የወደፊቱ ስክሪን ጥራት ማለት እኛ ምን እንደምናይ ብቻ ሳይሆን፣ ሌሎች ሰዎች ምን ማየት እንደሚችሉ መቆጣጠርም ነው።